ስለ እኛ

ኢማን ኢስላማዊ ማህበር የሙስሊሙን ህብረተሰብ መንፈሳዊና ማህበራዊ ችግሮች በመቅረፍና ኢስላማዊ አስተምሮን በማስፋፋት ሃላፊነት የሚሰማውና በኢስላማዊ እሴቶች የታነፁ እደዚሁም በሀገሪቱ ልማት ላይ ንቁ ተሳትፎ ያለው ዜጋን ለመፍጠር በሚደረገው ጥረት የበኩሉን አስተዋፆ ለማበርከት በ1995 ዓ.ል ተመስርቶ ለ17 አመታት በመልካም ስራዎች ላይ እየተሳተፈ የሚገኝ ተቋም ነው፡፡

በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የሚታዩት መጠነሰፊ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮችን አቅም በፈቀደ የመቅረፍ ሀላፊነት የሁላችም መሆኑን በመገንዘብ ዛሬነገ ሳንል የበኩላችንን እንወጣ በማለት እንቅስቃሴውን የጀመረው ማህበሩ ዛሬ ላይ በስፋት የሚታዩ በርካታ ተግባራት አከናውኖ ለቀጣይ ስራዎቹ መሰረት በሚሆን መልኩ እየሰራና ሌሎች መልካም አሳቢዎችን ከጎኑ በማሰለፍ ለተሻለ ውጤት እየተጋ ይገኛል፡፡

ኢማን ኢስላማዊ ማህበር ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ያማከለ ዕቅድ በመንደፍ የሚታዩትን ዘርፈ-ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ ስራዎቻችን በ4 ዋናዋና ዘርፎች በመደልደል ተንቀሳቅሷል ፡፡ እነዚህም፡-

 1. የእስልምና ጥናትና የአረብኛ ቋንቋ ትምህርት ተቋም ዘርፍ
 2. ማህበራዊ ቋሚ ድጋፍ ዘርፍ
 3. የኢስላማዊ ተቋማት ግንባታ ዘርፍ
 4. የዳዕዋ እና ቁርዓን መርከዞች ዘርፍ

በመባል የተዋቀሩ ሲሆን እነዚህ ዘርፎች በቅንጅትና በተናጠል ስራቸውን በአግባቡ እየተወጡ ይገኛሉ፡፡

ኑ! በጋራ ለማህበረሰባችን መልካምን እናድርስ!

ራዕያችን

 • የሙስሊሙን ማህበረሰብ መንፈሳዊና ማህበራዊ ችግሮች መቅረፍ
 • ኢስላማዊ አስተምሮን ማስፋፋት
 • ሀላፊነት የሚሰማውና በኢስላማዊ እሴቶች የታነፀ ዜጋ መፍጠር
 • በሀገራችን ልማት ላይ ንቁ ተሳትፎ ያለው ማህበረሰብ በመገንባት ረገድ ተቀዳሚ ማህበር መሆን

አላማችን

 • ሙስሊሙ ህብረተሰብ እምነቱን በሚገባ እዲያውቅ ማድረግና ማንነቱን ጠብቆ እዲኖር ማስቻል፤
 • የሀይማኖት አባቶችን (ኡለሞችን) በመንከባከብ እውቀታቸውንና ልምዳቸውን ለማህበረሰቡ እዲያካፍሉ ሁኔታዎችን ማመቻቸት፤
 • የተለያዩ ሐይማኖታዊ መፅኀፍትን፣ መፅሄቶችን፣ በራሪ ፅሁፎችንና ጋዜጦች፣ ሲዲዎችንና ሌሎችንም ኦዲዮቪዥዋል እንዲሁም የህትመት ውጤቶችን ማዘጋጀት፣ ማባዛትና በነፃ ማሰራጨት፤
 • የኢስላምን አስተምህሮ ቀላል፣ ምቹና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ማድረስ፤
 • የሀገራችንን አሊሞችና ዱዓቶች አስተሳሰብና የዕይታ አቅም ማሳደግ፤
 • የሸሪዓን ትምህርት ለተተኪው ትውልድ በተደራጀና ዘመናዊ በሆነ መንገድ ማድረስ፤
 • የሙስሊሙን ማህበረሰብ ችግሮች የሚፈቱ ጥናትና ምርምሮች ማካሄድ፤
 • ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል አሳታፊ የሆነ የዳዕዋና የስልጠና ፕሮግራሞችን ማመቻቸት (መፍጠር)፤
 • መድረሳዎችን፣ መስጊዶችን፣ መርከዞች እና ሌሎች ሃይማኖታዊ የትምህርት ማዕከላት የሚስፋፉበትና የሚጠናከሩበትን መንገዶች ማመቻቸት ፤ ውጤታማና ዘመናዊ እዲሆኑ ማስቻል፡፡
 • ውጤታማ የሆኑማ ህበራዊና ሀይማኖታዊ አገልግሎቶች ለሙስሊሙ ማህበረሰብ መስጠት፡፡

7040 Ok

አጭር SMS ፅሁፍ መልዕክት በመላክ

 • የመስጂድ ግንባታ
 • የሀይማኖት አባቶች(ኡለሞች) ድጋፍ
 • የቁርዓን ሂፍዝና ኢስላማዊ አስተምህሮ ተደራሽነት ማስፋት ላይ እንዲሁም ሌሎች ፕሮጀክቶችን በመደገፍ የመልካም ስራ አምባሳደር ይሁኑ!