ማህበሩ በሀገራችን እየከሰመ የመጣውን እና በባህላዊ መንገድ የወረስነውን የአረብኛና የእስልምና እውቀት ሽግግርን ለመታደግ ውጤታማና ዘመናዊ በሆነ መንገድ እውቀትን በማስተላለፍ መልካምና አገር ገንቢ የሆነ ማህበረሰብ ለመፍጠር ኢማን የተሰኘውን ኮሌጅ አቋቁሞ እየሰራ ይገኛል፡፡

ኢማንኢስላማዊማህበርያለመቺዉንሁለንተናዊለዉጥለማሳካትቁልፍመሳሪያእዉቀትእንደሆነታምናለች :: በዚህምየመጪዉንዘመንተግዳሮቶችለማሻገርብቃትያላቸዉምሉእእናሚዛናዊየኢስላምአስተምህሮያነገቡተማሪዎችንመፍጠርመቻልጊዜሊሰጠዉየማይገባጉዳይመሆኑንበማመንለዚህአላማመሳካትይረዳትዘንድበዉስጧኢማንየእስልምናጥናትናየአረበኛቋንቋተቋምንአዋቅራለች።

ከዚህተቋምዋናአላማዎችመካከልሙስሊሙህብረተሰብእምነቱንበሚገባእንዲያዉቅበማድረግየሃይማኖትአባቶችንማለትምምሁራንንበመንከባከብእዉቀታቸዉንናልምዳቸዉንለህብረተሰቡእንዲያካፍሉሁኔታዎችንማመቻቸት፤የተለያዩሃይማኖታዊመጽሃፍትን፣መፅሄቶችን፣በራሪፅሁፎችን፣ጋዜጦችን፣ሲዲዎችንናሌሎችንምየኦዲዮቪዥዋልናየህትመትዉጤቶችንበማዘጋጀትበነፃማሰራጨት፤እንደዚሁምየቁርአንንባብሂፍዝናመሰረታዊየኢስላማዊትምህርትበመድረኮችናመርከዞችዉስጥህጻናትናወጣቶችንማስተማር፤ኢስላማዊእዉቀትለሁሉምተደራሽይሆንዘንድዘመኑባመቻቻቸውየማስተማሪያዘርፎችሁሉበመገኘትእውቀትንእንካችሁእያለችትገኛለች።

ኢማንየእስልምናጥናትናየአረበኛቋንቋተቋምከተቋቋመጊዜአንስቶበርካታእዉቀትፈላጊዎችንበቀን፣በማታ፣በርቀትእንዲሁምበክረምትመርሃግብርፕሮግራሞችንበማዘጋጀት 74 መሻኢኾችንበዲፕሎማ፣ 30 መሻኢኮችንበሰርተፍኬትና 531 ተማሪዎችንበሰርተፊኬትእንዲሁምበክርምትኮርስ 4000 ተማሪዎችንአስመርቋል።አሁንም 1300 ተማሪዎችንበማስተማርላይይገኛል።600 ለኡለሞችአጫጭርስልጠናእና 105 ደግሞሸሀዳሰነውያበማስተማርላይይገናል።በተጨማሪምየሙስሊሙንማህበረሰብየእዉቀትጥማትለማርካትማንኛዉምሰዉባለበትቦታሁኖርቀትሳይገድበዉትምህርቱንእንዲከታተልኦንላይንትምህርት (online)www.iiias.com የተሰኘድረገፅ (ዌብሳይት)ዲቨሎፕበማድረግየመማሪያስርአትዘርግቶለማስተማርዝግጅቱንጨርሷል።

ከዚህምበተጨማሪበአብዛኞቻችንትኩረትለተነፈጉየህብረተሰባችንክፍሎችልዩትኩረትበመስጠትበልዩፍላጎትትምህርትፕሮግራምመስማትየተሳናቸዉንተማሪዎችበመሰረታዊየእስልምናእዉቀቶችየማነፅስራበመስራትላይይገኛል።ምንምእንኳበዘርፉያሉመምህራንቁጥርየለምሊባልበሚያስችልደረጃቢሆንምባለዉየሰዉሃይልለነዚህወንድሞችናእህቶችልንደርስላቸዉይገባልበማለትኢማንደፋቀናማለትከጀመረችሰነባብታለች፤ወደፊትምየመምህራንንእጥረትለመቅረፍየምልክትቋንቋስልጠናበመስጠትላይትገኛለች።አስካሁንም 25 ተማሪዎችንአስመርቃለች።    

“ብዙመስማትየተሳናቸዉከወላጆቻቸዉጋርያለዉችግርምንድንነዉወላጆቻቸዉቋንቋዉንአይችሉትምናምንምሊያስተላልፉላቸዉምሆነሊያስተምሯቸዉአይችሉም።ይህምአንድችግርነዉ።ቋንቋንቢማሩለዙህይጠቅማልሌላዉደግሞብዙክፍለሃገርላሉመስማትየተሳናቸዉተማሪዎችአሉአካዳሚክምሆነዲንትምህርትያልደረሳቸዉአሉ።አነሱንምመርዳትመቻልአለብን።ሌላዉደግሞቲቪምሆነየተለያዩሚዲያዎችንማየትአንችልምይህንንነገርደግሞሚሰሙሰዎችቢኖሩናቢተረጉሙልንለኛተደራሽነትይኖረዋል።መስጊድዉስጥምበምንገባበትጊዜምየሚሰሙሰዎችተሰባስበዉኮሚኒኬትያደርጋሉ።ቁርአንናሃዲስይቀራሉእኛግንእነሱንከማየትዉጪምንምልንጠቀምአልቻልንም።ብዙመስማትየተሳናቸዉደግሞቁርአንንመቅራትአልቻልንምይህንንምየሚሸፍንልንሰዉየለም።የሚሰሙሰዎችሲማሩእንደምናየዉከሆነትንንሽልጆችበትንሽደረጃከስርጀምሮይቀራሉ።ከዛምከፍእያሉይቀራሉ።እኛግንአንደኛነገርአሁንምቢሆንከህፃንነትይዞየሚስቀራንስለሌለየተቀላቀልንነዉየሚሆነዉ።ይህነገርራሱየመማርፍላጎታችንንእያመጣዉአይደለም።ስለዚህበደረጃየሚሆንትምህርትቢመጣልንየተሸለነዉ።”

በቅርቡለአይነስዉራንተመሳሳይየትምህርትእድልለማመቻቸትእቅድተይዟል።

ኢማንየእስልምናጥናትናየአረበኛቋንቋተቋምበመደበኛተከታታይናየርቀትትምህርትፕሮግራሞበመዘርጋትተቋሙየራሱንየመማሪያሞጁልማለትምመማሪያመጽሃፍበአማርኛቋንቋበማዘጋጀትለ 700 ተማሪዎችየርቀትትምህርትእየሰጠይገኛል።እንዲሁምኢንተርኔትመጠቀምለሚችልማንኛዉምሰዉባለበትቦታሁኖእዉቀትንእንዲገበይለማድረግበአገራችንናበመላዉአለምበርካታየፈተናጣቢያዎችንበመክፈትየኦንላይንትምህርት (online) ፕሮግራምንእንካችሁበማለትላይይገኛል።

የኮሌጃችን ራዕይ

በእስልምናና አረብኛ ጥናት ረገድ ተቋሙን ተቀዳሚና ተመራጭ የጥናትና ትምህርት ማዕከል ሆኖ ማየት፤

የኮሌጃችንዓላማ

የመጪውን ዘመን ተግዳሮቶች ለመሻገር ብቃት ያላቸው፣ምሉዕና ሚዛናዊ የኢስላም አስተምህሮን ያነገቡ ተማሪዎችን መፍጠር መቻል፤

በዚህ ዘርፍ የተከናወኑ ዋናዋና ተግባራት

•     151 ተማሪዎችን በአድቫንስድ ዲፕሎማ በርቀት መርሀ-ግብር አስመርቋል፡፡

•     (www.iiias.com) የተሰኘ ድህረ-ገፅ እና ኢማን ኢስላማዊ ኮሌጅ በሚል የሞባይል መተግበሪያ 165 ተማሪዎች በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

•     134 መሻኢኮች በዲፕሎማ ፕሮግራም አስመርቋል፡፡

•     105 ዑለሞች በሸሀዳ ፕሮግራም አስመርቋል፡፡

•     1205 መደበኛ ተማሪዎች በሰርተፊኬት ፕሮግራም አስመርቋል፡፡ •     ለ4581 ሁለተኛ ደረጃ እና ኮሌጅ ተማሪዎች የክረምት ስልጠና ሰጥቷል፡፡

የድህረገፅትምህርት

•ተማሪዎች ባሉበት ቦታ ሆነው ከአንጡራው ኢስላማዊ እውቀት ያሻቸውን ያህል መገብየት የሚችሉበት ዘመኑን የሚመጥን እና በቀላሉ ተደራሽ የሆነ  እውን ማድረግ ችሏል፡፡

•በየትኛውም የአለም ክፍል ላሉ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ማግኘት ለሚችሉ ሁሉ የተመቻቸ ነው !!

አላማው

•በየትኛውም የአለማችን ክፍል ውስጥ ያሉ የመማር ፍላጎት ላላቸው ግለ-ሰቦች ኢስላማዊ እውቀትን በቀላሉ ተደራሽ ማድረግ፤ •ወቅቱ የሚጠይቀውን የተማሪዎችን የትምህርት ፍላጎትና የግንዛቤ ፍጥነትን ባገናዘበ መልኩ ማስተማር የሚቻልበትን መንገድ ማመቻቸት፤

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here