ኢማን ኢስላማዊ ማህበር የሙስሊሙን ህብረተሰብ መንፈሳዊ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ችግሮችን በመቅረፍና ኢስላማዊ አስተምሮ በማስፋፋት ሃላፊነት የሚሰማዉና በኢስላማዊ እሴቶች የታነፁ እንደዚሁም በሃገሪቱ ልማት ላይ ንቁ ተሳትፎ ያለዉ ዜጋን ለመፍጠር በሚደረገዉ ጥረት የበኩሏን አስተዋፆ ለማበርከት ከዛሬ 18 አመት በፊት ግንቦት 1995 ዓ.ል ተመሰረተች።

            በተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች የሚታዩትን መጠነ ሰፊ የሙስሊሙ ማህበረሰብ ችግሮች አቅም በፈቀደ የመቅረፍ ሃላፊት የሁላችንም መሆኑን በመገንዘብ ዛሬ ነገ ሳንል የበኩላችንን እንወጣ በማለት እንቅስቃሴዋን የጀመረችዉ ኢማን እነሆ በዛሬዋ መድረክ የምናያቸዉን በርካታ ተግባራት አከናዉና በቀጣዩ ስራዎችም ስንቅ ለመቋጠር ሌሎችን ከጎኗ ለማሰለፍ ደፋ ቀና እያለች ትገኛለች።

ኢማን ኢስላማዊ ማህበር ከተመሰረተችበት ጊዜ አንስቶ ሁሉንም የማህበረሰብ ክፍል ያማከለ እቅድ በመንደፍ የሚታዩትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች ለመቅረፍ ስራዎችን በ4 ዋና ዋናዘርፎች በመደልደል ትንቀሳቀሳለች። በዚህም የእስልምና ትምህርት ዘርፍ፣የቁርአን ሂፍዝና የመርከዞች አስተዳደር ዘርፍ፣ የኢስላማዊ ተቋማት ግንባታ ዘርፍ፣በዳዕዋና ማህበራዊ ግልጋሎት ዘርፍ የተዋቀሩት ክፍሎች ስራቸዉን በአግባቡ እየተወጡ ይገኛሉ።

SHARE
Next articleኢማን ኢስላማዊ ኮሌጅ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here