በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ሙስሊሙ ማህበረሰብ ኃይማኖታዊ ተግባራቱን መፈፀም ይችል ዘንድ መስጂዶችና መድረሳዎች መኖራቸው አስፈላጊ መሆኑን በማመን ኢማን ኢስላማዊ ማህበር ክፍተቱን ለመሸፈን የኢስላማዊ ተቋማት ግንባታ በሚል ዘርፍ ስር የተለያዩ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ዘርፍ በተለይ በክልል ከተሞች የሚታየዉን የመስጅዶች፣የመድረሳዎችና የሂፍዝ ማእከላትን ከፍተኛ እጥረት ግምት ዉስጥ በማስገባት ችግሩ ጎልቶ የሚታይባቸዉን አካባቢዎች በጥናት በመለየት ክፍተቱን በዘላቂነት ለመዝጋት በርካታ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ይገኛል።

በእስከ ዛሬዉ እንቅስቃሴም በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች 26 መስጅዶችን አስገንብቶ ለማህበረሰቡ አበርክቷል። በአሁኑ ሰዓትም 15 መስጅዶችን በመገንባት ላይ ይገኛል።ለ 106 መስጅዶች ደግሞ የእድሳት፣የጥገናና የማስፋፊያ ስራ ተከናውኗል።

ኢማን በዚህ ሳትዎሰን 3 የቁርአን ሂፍዝ ማእከላትን አስገንብታ ለአገልግሎት ያበቃች ሲሆን 3 መርከዞችን ደግሞ በመገንባት ላይ ትገኛለች።እንዲሁም በአይነቱና በይዘቱ ለየት ያለ የመድረሳና የስልጠና ማእከልም እያስገነባች ትገኛለች።ወደ ፊትም እነዚህን የግንባታ ፕሮጀክቶች ችግሩ ወደ ተባባሰባቸዉ ቦታዎች በማስፋፋት የሙስሊሙን ህብረተሰብ የማእከላትና የመስጅድ እጥረት ለመቅረፍ ተግታት ሰርታለች።

በዚህ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት

በክልል ከተሞች የሚታየውን የመሳጂዶች፣የመድረሳዎችና የሂፍዝ ማዕከላት ከፍተኛ እጥረት በመቃኘትና በጥናት በመለየት፤ ክፍተቱንም በዘላቂነት ለመዝጋት ተንቀሳቅሰናል፡፡

በዚህም በሀገሪቱ የተለያዩ ክልሎች

•     42 መስጂዶችን አስገንብቶ ለማህበረሰቡ አበርክቷል፡፡

•     ከ106 በላይ መስጂዶችን የእድሳት ስራዎችን ማከናወን ተችሏል፡፡

•     6 የቁርዓን ሂፍዝ ማዕከላት በማስገንባት ለኡማው ተበርክቷል፡፡

•     በአይነቱ የተለየ በ740ካ.ሜ ላይ ያረፈ መስጂድ፤ 250 ካ.ሜ ት/ቤት፤ 500ካ.ሜ ወርክሾፕ እና 246ካ.ሜ ላይ ያረፉ 6 የኡስታዞች መኖሪያ ቤቶች በዱከም ከተማ ተገንብቷል፡፡

•     በቢሾፍቱ ከተማ በይዘቱ ትልቅ የሆነ መስጊድ ተገንብቶ ለማህበረሰብ ክፍት ሆኗል፡፡

•     በሊሳና ከተማ ት/ቤት፣ መመገቢያ፣ ማደሪያና የመምህራን ማረፊያ የያዘ 519ካ.ሜ ላይ ያረፈ ግዙፍ ሁለ-ገብ ማዕከል በመገንባት አስመርቀናል፡፡

•     በቦኢሻ ከተማ 193ካ.ሜ ላይ ያረፈ መድረሳ በመገንባት አስመርቀናል፡፡

የተቋማት ግንባታ

•     በሀገራችን በተለያዩ ከተሞች ከ100 በላይ መስጂዶች ግንባታ፣ ማስፋፊያና ጥገና ተደርጎላቸዋል፡፡

•     የመስጂድና መድረሳዎች ከተገነቡባቸው ከተሞች መካከል

ሀዲያ ; ስልጤ ; ሀላባ; ዓፋር; ወረባቡ; ሀጤሳ; ሰንበቴ; ያቤሎ; ከረዩ; እነሞር; ወለኔና አቅስታ …ሲሆኑ

•     በሀዲያ ሊሳናና ዶኤሻ

•     በአዲስ አበባ ዙሪያ ዱከምና ቢሾፍቱ •     ግዙፍና ሁለ-ገብ ማዕከላትንና መስጂዶች ተመርቀው አገልግሎት እንዲሰጡ ተደርጓል፡፡

የዑለማ ድጋፍና ኪታቦች ስርጭት

ብርቅዬ ዑለሞቻችን በኢኮኖሚ ችግር ምክኒያት እዳይፈልሱና እዳይሰደዱ ኢማን ቋሚ ድጋፍ እሚያገኙበት ሁኔታ እያመቻቸና በቋሚነት ድጋፍም እየሰጠ ይገኛል፡፡

በተጨማሪም፡-15,965 የተለያየ መጠን ያላቸው ቁርዓኖች

14,000 በላይ የተለያዩ ኪታቦችን በገጠር ለሚገኙ መድረሳዎች፣ መሻኢኮች እና ደረሳዎች እንዲከፋፈል ተደርጓል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here