የዳዕዋ እና ቁርዓን መርከዞች ዘርፍ

0
512

ቁርዓንን ማስተማር እና የቁርዓን መምህራንን ማፍራት ሙስሊሙን ማህበረሰብ ለሀይማኖቱ ያለውን ግንዛቤ ለማነፅ እጅጉን አስፈላጊ ነው፡፡በመሆኑም እየመነመነ የመጣውን ኢስላማዊ እውቀት ስርጭትን ለመታደግ የዳዕዋ እና ቁርዓን መርከዞች ዘርፍ በማቋቋም በርካታ ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በሃገራችን ያለዉን የቁርአን ሂፍዝ ተማሪዎች እጥረትና ትምህርቱን ለማግኘት የሚሰጥባቸዉ መርከዞች አለመበራከትን ግምት ዉስጥ በማስገባት በተለያዩ አካባቢዎች 7 መርከዞችን (የቁርአን ሂፍዝ ማዕከሎችን) በመክፈት 587 የቁርአን ሂፍዝና ነዝር ተማሪዎችን ሲያስተምር የነበረ ሲሆን ከነዚህም ዉስጥ 78ቱ ሙሉ ቁርአንን ሃፍዘዉ ተመርቀዋል። አሁን ደግሞ 206 ተማሪዎች ሂፍዝ ሲማሩ 303ቱ ደግሞ ነዝር ተማሪዎች ናቸው።

ሂፍዝ ማዕከሎቹ የሚገኙት በሃዲያ፣ በስልጢ በኦሮሚያና እንዲሁም በአዲስ አበባ ነው።

በዚህ ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት

  • የቁርዓን አስተምህሮት በተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ከረዩ፣ያቤሎ፣ ሀድያ እና አዲስአበባ 960 ተማሪዎች ባሳለፍነው አመት ማስተማር ተችሏል::
  • በረመዳን ኢፍጣር እና የኮቪድ-19 ብሸታ ለመከላከል ለ20300 ግለሰቦች ተደራሽ በመሆን ማህበራዊ ሃላፊነትን የመወጣት ስራ ተሰርቷል::
  • የቤት ለቤት ድጋፍ ለኩላሊት ታማሚዎች፣የካንሰር ታማሚዎች እና በተለያዩ ምክንያቶች ቤት ለቀሩ ግለሰቦች ድጋፍ የማድረግ ስራ ተሰርቷል::
  • በከረዩ እና ያቤሎ ማህበረሰብ 610 ግለሰቦችን ወደ እስልምና የመጥራት ስራ ተሰርቷል::
  • በልዩ ሁኔታ በሰበታ ክፍለ ከተማ ለ200 ማየት ለተሳናቸው የማህበረሰብ ክፍሎች የአሰቤዛ እና የንፅህና መጠበቂያ ድጋፍ ተደጓል::
  • ለተቸገሩ ወገኖች አረፋን በደስታ መዋል እንዲችሉ ለ6000 ግለሰቦች የኡዱህያ ስጋ የማከፋፈል ስራ ተሰርቷል፡፡

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here